የኢትዮጵያዉያን ሁኔታ በሳዑዲ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2006ማስታወቂያ
በጂዳ የዶቼ ቬለ ዘጋቢ ነብዩ ሲራክ እንደሚለዉ የሳዉዲ መንግስት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸዉ የዉጭ ዜጎች ከሀገሩ እንዲወጡ የጀመረዉ ዘመቻ ተጠናክሯል። ቆንስላዉ አስተላለፈ የተባለዉን ማሳሰቢያ አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን በአጭሩ ጠይቀናል፣
እንደየጂዳዉ ዘጋቢያችን ነብዩ ሲራክ ከሆነ ወደሳዑዲ በባህር፤ በሃጅና ኡምራ፤ በጉብንትና በሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የገቡት ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ይህን ያህል ነዉ ብሎ ለመናገር ለጊዜዉ ያዳግታል። በጥብቅይተገበራልተብሎየሚጠበቀዉ የሳውዲሕግ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸዉን ብቻ የሚመለከት አይደለም። ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ይዞ ከአሰሪው ጋር የማይሠራ ከሃገር ይውጣ መባሉ ሌላዉ የስጋት ምንጭ ሆኗል። ስለሁኔታዉ እንዲያብራራልን ነብዩን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ ጠይቄዋለሁ፤
ነቢዩ ሲራክ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ