የኢትዮዽያ ብር ከዶላር አንጻር ዋጋው በ17 በመቶ ቀነሰ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 27 2002ማስታወቂያ
የኢትዮዽያ መንግስት የብርን የመግዛት አቅም በ17 በመቶ ዝቅ እንዲል ያደረገ ውሳኔ ትላንት አስተላልፏል። መንግስት ይህን ውሳኔ ያስተላለፈበትን ምክንያት በዝርዝር አልገለጸም። በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮዽያ ተወካይ፤ ኢትዮዽያ ወደውጭ በምትልካቸው ምርቶች ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድግ ውሳኔ ሲሉ ገልጸዋል። ይህ በብር የመግዛት አቅም ላይ በከፍተኛ መጠን ዝቅ እንዲል የተደረገበት ውሳኔ በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶች አየተሰጡበት ነው። በቺካጎ ሀርቨር ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ መምህር ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ከዓለም ዓቀፍ ባንክና ከገንዘብ ተቋማት በተደረገ ግፊት መንግስት እርምጃውን ወስዷል ሲሉ ይናገራሉ። ይህ እርምጃ ግሽበትን የሚያባብስ፤ የኢኮኖሚውን ቀውስ የሚያጠናክር፤ ደሀውን ህዝብ የበለጠ የሚጎዳ ነው ብለዋል--ፕሮፌሰር ጌታቸው።
መሳይ መኮንን
ሂሩት መለሠ
ሸዋዬ ለገሠ