የኢራን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣
ሐሙስ፣ ሰኔ 4 2001ማስታወቂያ
በእጩነት የቀረቡት ተወዳዳሪዎች ፣ በኢራን አብዮት ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸውና በአገሬው ህዝብ ዘንድ የተከበሩ በመሆናቸው፣ ውድድሩን ጠንካራ ሊያደርገው እንደቻለ ፣ የፖለቲካ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ከ 4ቱ ተወዳዳሪዎች መካከል ዋንኞቹ ፕሬዚዳንት ማህሙድ አህማዲነጃድና የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ሚር ሁሴን ሙሳቢ ሲሆኑ፣ ሁለቱ፣ በቴሌቭዥን ባደረጉት ክርክር ፣ በውጭ ግንኙነት፤ በኑክልየር ፣ በማኅበራዊ ኑሮ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ ሲሆን፣ የ «ምረጡን» ዘመቻ ባካሄዱባቸው 4 ሳምንታትም ፤ ደጋፊዎቻቸው አደባባይ በመውጣት የቅስቀሳው ተሳታፊዎች ሆነዋል።
---ነቢዩ ሲራክ---
ተክሌ የኋላ/ሸዋዬ ለገሠ