የኢራን እና ስድስቱ ታላላቅ መንግስታት ምክክር
ዓርብ፣ መስከረም 22 2002ማስታወቂያ
ዉይይቱ በመግባባት መከናወኑ እና በመቀጠል በቅርቡ እንደገና ዉይይት ለማድረግ መስማማታቸዉ ተዘግቦአል። ከዚሁ ጎን ለጎን ላላፉት 30 አመታት በባላጣነት ይተያዩ የነበሩት የአሜሪካ እና የኢራን መንግስታት ተደረዳሪዎች፣ የተናጠል ዉይይት ማድረጋቸዉ ተጠቁሞአል። ይህም ሆኖ ከኢራን ስለሚጠበቀዉ የኑክልየር ጣብያን ማስፈተሽም ሆነ፣ በቅርቡ ይፋ የሆነዉ የኑክልየር ጣብያ የዉይይቱ ዋንኛ የመነጋገርያ አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ቢገመትም፣ በዚህ ረገድ ተደራዳሪዎች ስለደረሱበት ስምምነት ይፋ የወጣ መግለጫ አለመኖሩ ተነግሮአል። ዝርዝሩን የሳዉዲአርብያዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ልኮልናል።
ነብዩ ሲራክ ፣ አዜብ ታደሰ፣ አርያም ተክሌ