የኢራን ምርጫ ውጤት ያስከተለው ውዝግብ ና ግጭት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 9 2001ማስታወቂያ
ድምፅ ቆጠራው ተጭበርብሯል የሚሉት የዕጩ ፕሬዝዳንት ሚርሆሴን ሙሳቪ ደጋፊዎች ተቃውሞአቸውን በመላ ኢራን በተለያየ መንገድ እየገለፁ ነው ። በዋና ከተማይቱ በቴህራን በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ የሙሳቪ ደጋፊዎች ትናንት አደባባይ በመውጣት አመፅ የተቀላቀለበት ተቃውሞ አካሂደዋል ። ያለ መንግስት ፈቃድ በተካሄደውና ዕጩ ተወዳዳሪ ሙሳቪ በተገኙበት በዚሁ የተቃውሞ ሰልፍ መንስኤም የሰባት ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ። መንግስት የአመፁ ቆስቋሽ ናቸው ያላቸውን ሰዎች እያሰረ ነው ።
ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ