የኢራቅ መንግስት ሞሱልን መቆጣጠሩን አስታወቀ
እሑድ፣ ሐምሌ 2 2009ማስታወቂያ
የኢራቅ መንግስት የሞሱል ከተማን በድጋሚ ለመቆጣጠር ዘመቻ የከፈተችው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር፡፡ የኢራቅ ጦር ስድስተኛ ክፍለጦር መሪ ሌተናል ጃሲም ኒዛል እንደተናገሩት የእርሳቸው ወታደሮች ድል አድርገዋል፡፡ ወታደሮቹ በታንኮች ላይ ሆነው ድላቸውን በዳንስ እና በዘፈን በሚገልጹበት ወቅት በአቅራቢያቸው የአየር ጥቃት መቀጠሉን አሶሴትድ ፕሬስ ከስፍራው ዘግቧል፡፡ እንደ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትር አባዲ የሞሱልን በድጋሚ በቁጥጥር ስር መዋል ለማወጅ በቦታው በተገኙት ወቅት እንኳ ውጊያ ይካሄድ ነበር፡፡
በሞሱል በመንግስት ወታደሮች እና ታጣቂዎቹ መካከል ወራትን የፈጀው ከባድ ውጊያ በርካቶችን ለሞት የዳረገ ሲሆን 900 ሺህ ገደማ ነዋሪዎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል፡፡ የሞሱል አብዛኛው ክፍል እና በዙሪያ ገባው ያሉ አካባቢዎቹን በውጊያው መውደማቸውን የዜና ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡
ተስፋለም ወልደየስ
ልደት አበበ