የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ፤ ያሸንፋሉ ተብለዉ የሚጠበቁ ቡድኖች
የዘንድሮዉን አፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥምያ አሸናፊ ኮትዴቮአር ናት ሲሉ ከወዲሁ የዘርፉ ባለሞያዎች መላምታቸዉን እየሰጡ ነዉ። የሌሎች አፍሪቃ ሃገራት ብሔራዊ ቡድኖችም ቢሆን ዋንጫዉን የማግኘት ጥሩ ተስፋ አላቸዉ።
ጠንካሮቹ ዝሆኖች
የጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ.ም አፍሪቃ እግር ኳስ ግጥምያ አሸናፊዎች የዘንድሮን ዋንጫ ይወስዳሉ ተብሎ ከሚገመቱት ቡድኖች መካከል ቀዳሚዉን ስፍራ ይዘዉ ይገኛሉ። ምንም እንኳ የ «ወርቃማዉ» ትዉልድ ተጫዋቾች ዲደየር ድሮግባና ያያ ቱሬ ቡድኑን ለቀዉ ቢወጡም፤ የኮት ዲቯር አሰልጣኝ ሚሻኤል ዱሱየር በቡድኑ ምርጥ የሚሏቸዉን አንድ ሁለት ብለዉ መቁጠር ይችላሉ። የኮት ዲቯሮቹ ዝሆኖች ሁሉም ማለት ይቻላል እንደስያሜያቸዉ ሁሉ ዳጎስ ያለዉን ደሞዛቸዉን የሚያገኙት በአዉሮጳ ቡድኖች ዉስጥ በአጥቂነት ተሰልፈዉ በመጫወት ነዉ። ለምሳሌ ዊልፍሬድ ቦኒ«ቀኝ»፤ ዊልፍሪድ ዛሃ ፤ ኤሪክ ባጂን መጥቀስ ይቻላል።
የመጀመርያዉ የድል ሕልም
በፊፋ የዓለም ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋች ቡድን መዘርዝር 33ኛ ላይ የሚገኘዉ የሴኔጋሉ ብሔራዊ ቡድን በአሁኑ ወቅት ጠንካራና ምርጥ የአፍሪቃ የእግር ኳስ ቡድን ነዉ። ሳዲዮ ማኔ «ግራ» በእንግሊዙ ፕሪሜር ሊግ ከሊቨርፑል ጋር ዉል ተፈራርሞአል። የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ባልደረቦቹ በበኩላቸዉ በዚህ የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያ ላይ ለአገሩ ተሰልፎ በአሸናፊነት ዋንጫዉን ወደሃገራቸዉ ማስገባት ይፈልጋሉ። ሴኔጋል እስካሁን ከተካሄዱት የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያዎች መካከል በጎርጎሮሳዉያኑ 2002 ዓ.ም በሁለተኛነት በማጠናቀቅ ጥሩ ዉጤት አስመዝግባለች።
ክንፋሙ ግሥላ
የጋቦን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች፤ ደጋፊዎቻችን ክንፍ ሊያዉሱን ይችላሉ የሚል ተስፋን ሰንቀዋል። ግሥሎቹ ከስከዛሬዉ የአፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥምያ ከሩብ ፍጻሜ አልፈዉ አያዉቁም። የጋቦን የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በተለይ በብሔራዊ ቡድኑ አጥቂ በፒየር ኤሜሪክ አዉባሜያንግ «ግራ» ላይ ተስፋቸዉን ጥለዋል። ፒየር በጀርመኑ «ቡንደስሊጋ» ለቦርስያ ዶትርሙንድ ተሰልፎ 16 ግቦችን በማስቆጠር በድንቅ አጥቂ ተጫዋች መዘርዝር ዉስጥ ተመዝግቧል።
ዳግም ለማሸነፍ ማሪዝን መያዝ ?
በጎርጎረሳዉያኑ 2014 ዓ.ም የተካሄደዉ የዓለም የእግር ኳስ ጨዋታ ትዝታ የሚጠፋ አይደለም። ብራዚል ላይ በተካሄደዉ በዚህ ግጥምያ ሩብ ፍጻሜ የደረሰዉ የአልጀርያዉ ቡድን፤ በግጥምያዉ ቆየት ብሎ ዋንጫዉን እጁ ያስገባዉን የጀርመንን ቡድን ማንገዳገዱ ይታወሳል። በበረሃማዋ አልጀርያ ያደገዉ የቡድኑ አጥቂ ሪያድ ማህሬዝ «ግራ» በቅርቡ የአፍሪቃ የዓመቱ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች በመባል መሸለሙ ይታወቃል። አልጀርያ ለመጀመርያ ጊዜ በጎርጎረሳዉያኑ 1990 ዓ.ም የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያን ማሸነፏ ይታወሳል።
ጥቋቁሮቹ ኮከቦች ከሁለተኛነት ከፍ ማለትን ይሻሉ
ጥቋቁሮቹ ኮከቦች ደረጃን ጠብቆ ለማለፍ እንደ ባህላቸዉ ታዋቂዉን አጥቂ አንድሪ አየዉን ማስገባታቸዉ የተለመደ ነዉ። አንድሪ አየዉ ሦስት ግዜ የአፍሪቃ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሞአል። የጋና ብሔራዊ ቡድንም የአህጉሪቱን የእግር ኳስ ግጥሚያ ሦስት ጊዜ አሸንፎአል። ቢሆንም ቡድኑ የመጨረሻዉን የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያ ያሸነፈዉ የዛሬ 35 ዓመት ነዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ.ም በተካሄደዉ የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ግጥምያ ጋና ለመጀመርያ ጊዜ ለዋንጫ ቀርባ በፍጹም ቅጣት በኮት ዲቯር መሸነፍዋ ይታወቃል።
የፈርኦኖቹ መመለስ
በማሸናፍ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የአፍሪቃዉ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዉድድር ሜዳዉ ዳግም ተመልሶአል። በአፍሪቃ አህጉር የዋንጫ ግጥምያ ላይ ለመሳተፍ የማጣርያ ግጥምያን ሦስት ጊዜ ማለፍ ያልቻለዉ የግብፅ ቡድን ሰባት ጊዜ ዋንጫን በጁ ያስገባ ጠንካራ ቡድን ነዉ። ግብፅ ዘንድሮ በጋቦን የሚካሄደዉን ግጥምያ ለመሳተፍ ማጣርያዉን አልፋ ቀርባለች ሞሃመድ ሳላህን «ቀኝ 2ኛ» ጨምሮ ሌሎች ፈርኦኖች ልክ እንደ ጎርጎረሳዉያኑ 2010 ድል ሁሉ ዋንጫዉን ይዘዉ ይመለሳሉ የሚል ጠንካራ እምነት አለ።
የስኬታማነት ስልት ለስኬታማ አሰልጣኝነት?
እንደ እቅዱ ቢሆን ኖሮ የጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ,ም የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያ የሚካሄደዉ በሞሮኮ ነበር። ተነሳ የተባለዉን የኤቦላ ወረርሽኝ ተከትሎ ሞሮኮ፤ ጨዋታዉን ማስተናገድ ባለመፈለግዋ ግጥምያዉ በኢኳቶሪያል ጊኒ ተካሂዶአል። የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ግን በጫወታዉ እንዳይሳተፍ ታግዶ ነበር። ዘንድሮ ግን አዚዝ ቦሃዱዝ «ግራ» እና ባልደረቦቹ ጋቦን በሚካሄደዉ ግጥምያ ሜዳ የኳስ ጨዋታ ማለት እንዴት እንደሆነ ማሳየት ይፈልጋሉ። አሰልጣኝ ሃርቨ ሬንአርድ በዚህ አይታሙም፤ ምክንያቱም በጎርጎረሳዊዉ 2012 ዓ.ም የዛምቢያ አሰልጣኝ ነበሩ፤ በ2015 ደግሞ ኮት ዲቯርን ለዋንጫ አብቅቷል።