የአፍሪቃ ና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ግንኙነት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 1 2006ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ የተካሄደው አራተኛው የአፍሪቃ የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተነጋግሮ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች ውስጥ የሁለቱ ክፍለ ዓለማት የኤኮኖሚ ግንኙነት አንዱ ነበር ። የመሪዎቹ ጉባኤና እዚያው ብራስልስ የተካሄዱ ሌሎች ተጓዳኝ ስበስባዎች የሁለቱን ክፍለ ዓለማት የኤኮኖሚ አጋርነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲሁም ኤኮኖሚያቸውን ለማሳደግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን በመተለም ተጠናቀዋል ። በአሁኑ ወቅት የአፍሪቃና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ግንኙነት አዲስ አቅጣጫ እንዲከተል ያስፈለገበት ምክንያትና ጥቅሙ ምንድነው ? የኤኮኖሚ ግንኙነቱ በሁለቱ ክፍለ ዓለማት የፖለቲካና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይስ ምን ዓይነት ተፅእኖ ያሳድራል ? የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ በዛሬው ከኤኮኖሚው ዓለም ዝግጅት ከሁለቱ ክፍለ ዓለማት መሪዎች ጉባኤ ውሳኔዎችና መግለጫዎች ጋር እያገናዘበ የሚዳስሳቸው ጉዳዮች ናቸው ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ