የአፍሪቃ መሪ ሴቶች ጉባዔ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 19 2010የአፍሪቃ መሪ የሴቶች መረብ ትስስር « African Leader Womens Net-Work»በሚል ርዕስ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ የታመነበት ከአንድ ወር በፊት ኒዮርክ ላይ በሚገኘዉ በተመድ ዋና ፅፈት ቤት መዋቀሩ ታዉቋል። በአዲስ አበባ በአፍሪቃ ኅብረት ከየአባላቱ የተጋበዙ ሚና ያላቸዉ ሴቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ በመጠናቀቅ ላይ ያለዉ ጉባዔ ዋና መሰረተ ሃሳቡ ነዉ። ይህን በዝርዝር የገለፁት በመንግሥታቱ ጽ/ ቤት ምክትል ፀሐፊዋ አሚና መሃመድ ናቸዉ « ይህ የትስስር መረብ በተጠናከረ መልኩ ተዓማኒነት እንዲኖረዉ በሺዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካዉያን ሴቶች የሚሳተፉበት መሆን ይገባዋል በቀጣይ በምንገናኝበት ጊዜ ስለሴቶች በጥቅሉ ለማስረዳት አንደበት ይኖረናል። ህልማችን ተግባራዊ በሚሆንበት ለዝያዉ ለተነሳልነት ዓላማ በየሃገራችን የምንሰራበት ተግባር ነዉ የሚሆነዉ። በጋራ የምንወስደዉ አቅዋም የዉይይት መድረክ መከፈት እንደሚያስፈልግ ነዉ። በሃገራቱ መካከልም ሳይቀር አጋርነትና ዓባልነትንም በማካተት የሴቶችን የመሪነት ሚና በማረጋገጥ በልማት በኤኮኖሚዉ ግችትን ቀድሞ መከላከልን በፖለቲካዉ ተሳትፎ ፤ በአፍሪቃም ሴቶችን ከምርጫ በማግለል እየተደረገ ያለዉን በዚህ ሁሉ ላይ ነዉ የምንሰራዉ።» የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ቦታዉ ላይ ተገኝቶ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ