የአፍሪቃ መሪዎች ልዩ ጉባኤ ፍፃሜና ጋዳፊ ሥልጣን የያዙበት 40ኛ አመት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 2001ማስታወቂያ
የአፍሪቃ መሪዎች ትናንት ትሪፖሊ ሊቢያ ውስጥ ያካሄዱት ልዩ ጉባኤ በአፍሪቃ ለሚከሰቱ ቀውሶች ግጭቶች አስቸኳይ መፍትሄ መሻት የተመለከተ የድርጊት መርሀ ግብር በማውጣት ተጠናቋል ። በዚሁ መርሀ ግብር ላይ በሶማሊያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ለሚገኘው የአፍሪቃ ህበረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ወታደሮችን ለማዋጣት የተስማሙ ሀገራት ቃላቸውን እንዲያከብሩ ተጠይቀዋል ። ጉባኤው ላይ የተገኙት የአፍሪቃ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች የሊቢያው መሪ የሞአመር ጋዳፊን 40 ኛ ዓመት የስልጣን ዘመን አክብረዋል ። ዝርዝሩን ጌታቸው ተድላ ያቀርብልናል ።፡
Agenturen/Getachew Tedla,Hirut melesse
Negash Mohammed