የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ፍፃሜ
ማክሰኞ፣ ጥር 22 200418ኛው የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ፤ ባለፈው ሌሊት ተደምድሟል። የኅብረቱን ኮሚሽን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ሳይቻል ቀርቶ ፣ ጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ በመውሰዱ ፤ በመጨረሻ፤ ዣንግ ፒንግና ኮሚሽነሮቻቸው፤ ባሉበት ሥልጣናቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ተወስኗል። አንዳንድ ለየት ያሉ ሁኔታዎችም በጉባዔው ተከሥተዋል። ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ-----------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------------
የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ሁነኛ ዉሳኔ ያሳልፍባቸዋል ከተባሉት ጉዳዮች አንዱ የሶማሊያ ሠላምና ሶማሊያ የዘመተዉ የአባል ሐገራት ሠራዊት ነበር።ጉባኤዉ ዘመነ-ሥልጣናቸዉን ለስድት ወራት ያራዘመለቸዉ የሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ዣን ፒንግ ለጉባኤተኞች ባቀረቡት ዘገባ ሕብረታቸዉና አባላቱ በሶማሊያ ሠላም ለማስፈን የሚያደርጉት ጥረት ጥሩ ዉጤት ማሳየቱን ጠቅሰዉ ነበር።ይሁንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓ ጊ ሙንን ጨምሮ ጉባኤተኞች የሶማሊያን የወደፊት ሠላም እንዳይዘነጉ ቢያሳስቡም የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደዘገበዉ ከጉባኤዉ «ጠብ ያለ ነገር» የለም።ዝር ዝሩ እነሆ።
ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ-
ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የዋኋላ