1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሕብረትና ግብፅ

ሐሙስ፣ ሰኔ 12 2006

የአፍሪቃ ሕብረት ፣ የግብፅ ጦር ኃይል በወታደራዊ መፈንቀለ መንግሥት፤ የቀድሞውን በዴሞክራሲ የተመረጡትን ፕሬዚዳንት ከሥልጣን እንዲወገዱ አድርጓል በማለት ፣ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት መሥራች የሆነችውን ሀገር አንድ ዓመት ያህል ከአባልነት አግዶአት

https://p.dw.com/p/1CMUR
ምስል Ahmed Abu Dahb

መቆየቱ የሚታወስ ነው። ሕብረቱ፤ በተለይም የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ኮሚሽኑ ፤ ከትናንት በስቲያ ፣ ማክሰኞ ማታ በሰፊው ከተወያየ በኋላ፣ ትናንት መልሶ ተቀብሏታል። ጊኒ ቢሳዎንም መልሶ ተቀብሏል ። እልባት ያላገኘው የማዕከላዊት አፍሪቃ ሪፓብሊክ ጉዳይ ብቻ ነው። የአፍሪቃ ደንብ ፤ የአባል ሃገራት ፣ መንግሥታት በዴሞክራሲ የተመረጡ መሆን አላባቸው ይላል። በክፍለ ዓለሙ በጣት በሚቆጠሩት እጅግ ጥቂት ሃገራት በስተቀር ፤ በብዙዎቹ ዓለም አቀፍ መሥፈርትን በሚገባ ያሟላ ምርጫ ሲካሄድ አልታየም። የግብጽን ወደ አፍሪቃ ሕብረት መመለስ በተመለከተ ፤ ተክሌ የኋላ ፤ የአፍሪቃውን ቀንድ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ ዩሱፍ ያሲንን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ