የአፍሪቃ ሕብረትና የሶማሊያ ሠላም
ዓርብ፣ ኅዳር 8 2004ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ሕብረት ወደ ሶማሊያ ለማዝመት ላቀደዉ ሰወስት ሺሕ ተጨማሪ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት አባል ሐገራት ወታደሮች እንዲያዋጡ ለማግባባት የሚያደርገዉን ጥረት እንደቀጠለ ነዉ።የሕብረቱ የሠላምና የፀጥታ ኮሚሽን ትናንት አዲስ አበባ ዉስጥ ባደረገዉ ሥብሰባዉ እስካሁን ሞቃዲሾ ጦር ያሰፈሩት ዩጋንዳና ቡሩንዲ ተጨማሪ ወታደሮች ለማዋጣት መፍቀዳቸዉን ሲያስታዉቅ፥ ጂቡቲ አንድ ሻለቃ ጦር ለማዝመት ቃል መግባቷን ገልጧል።ኬንያ ደቡቡ ሶማሊያ ከሚዋጋ ጦሯ ሌላ የሠላም አስከባሪ መለዮ ያጠለቀ ጦር ለማዝመት እንደምትፈልግ አስታዉቃለች።የኢትዮጵያ አቋም አለየም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ