የአፍሪቃ ልማት እና የገጠመው ችግር
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 15 1998ማስታወቂያ
የሥራ አጥነት መስፋት በአፍሪቃ
ብዙ አፍሪቃውያት ሀገሮች የሚልየንየሙን የልማት ግቦች ለማሳካት ያላቸው ተስፋ እጅግ የመነመነ መሆኑ ተገልፆዋል። በተለይ፡ በወጣቱ ትውልድ መደዳ የተስፋፋው የሥራ አጥነት ችግር እና ያልሠለጠነው የሰው ኃይል በልማቱ ዘርፍ ሊሠማራ ያልቻለበት ድርጊት የአህጉሩን ልማት ወደኋላ እያስቀረው እንደተገኘ የተመድ የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ኮሚሽን ከጥቂት ጊዜ በፊት ባወጣው አንድ ዘገባው አስታውቋል።