የአገር አቀፍ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ዝግጅት
ዓርብ፣ የካቲት 8 2011ማስታወቂያ
በመጪው መጋቢት ወር ለሚካሄደው አገር አቀፍ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ሥራ አስፈላጊውን መሰናዶ ማጠናቀቁን የፌደራል ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው በተለይ ለዲ ደብሊው እንዳስታወቀው የቆጠራ ሥራው የሚካሄድባቸው እንደ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ የቆጠራ ካርታ ቦታዎች ተለይተው ተዘጋጅተዋል፡፡ በቆጠራ ውጤቱ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችን ለመቀነስ የቆጠራው ሂደት በዲጂታል ቴክኖሎጂ በተጋዘ መንገድ እንደሚከናወን የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሳልፈው አበራ ገልጸዋል፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ