የአድዋ የድል በአል በፍራንክፈርት
ማክሰኞ፣ መጋቢት 3 2011ማስታወቂያ
ይህን የገለፁት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአሁኑ ወቅት ግን የሚታየው ዘርን እና ቋንቋን ያማከለ አደረጃጀት በአገሪቱም ሆነ በሕዝቦቿ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን ጠቁመዋል። በዚሁ ሥነ ሥርዓት የተካፈሉት በኢትዮጵያ ኤምባሲ የፍራንክፈርት ቆንጽላ ጽሕፈት ቤት ተወካይ አምባሳደር በረደድ አንሙት በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን የተጀመረውን ለውጥ ለማጠናከር ተሳትፎአቸውን አጠንክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። የዝግጅቱ ታዳሚዎች በኢትዮጵያ የሚታየው የብሔር ግጭት እና የሕዝቦች መፈናቀል አሳሳቢ መሆኑን በመግለጽ መንግሥት ለችግሩ አፋጣኝ እልባት ሊያበጅለት እንደሚገባ በበኩላቸው አሳስበዋል። በዝግጅቱ ላይ የተገኘው እንዳልካቸው ፈቃደ ዘገባ ልኮልናል።
እንዳልካቸው ፈቃደ
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ