የአድዋ ቤተ መዘክር
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9 2006ማስታወቂያ
በአድዋ ከተማ የአድዋን ታሪክ ቤተ መዘክር ፣ የኢትዮጵያ የታሪክ ምርምር ማዕከልና ቤተ መፃህፍት የሚያካትት ህንፃ ግንባታ 50 በመቶ መጠናቀቁ ተገለፀ ። በአንድ ባለሃብት በመቶ ሚሊዮን ብር ወጪ በመሰራት ላይ ያለው ይኽው ግንባታ በሥራ ሂደት ብዙ ውጣ ውረዶች ቢገጥሙትም ግንባታው እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሃንስ ገብረ እግዚአብሄር ዘግቧል ። ባለሃብቱ ብዙዎች ጥናትና ምርምር ለመጀመር በጉጉት የሚጠብቁትን የህዝብ ንብረት የሚሉትን ይህን ግንባታ ከፍፃሜ ለማድረስ በመጣር ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል ። ዝርዝሩን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር አዘጋጅቶታል ።
ዮሃንስ ገብረ እግዚአብሄር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ