የአዲስ ሥነ ቴክኒክ ግኝቶች ባለቤት
ረቡዕ፣ ጥር 23 2004ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዊ የፊዚክስ ፕሮፌሰር ጋር ባደረግነው ጭውውት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ተማሪዎች፤፣ ወጣቶች የሳይንስ ትምህርትን ይወዱ ዘንድ ስለማነቃቂያው መላ ፤ ጠይቀናቸው እንደነበረ ይታወስ ይሆናል። ለፕሮፌሰር ሰሎሞን ቢልልኝ ፣ ያን ጥያቄ ማቅረባችን፣ (ያቀረብነው)ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ፤ ለታዳጊ አገሮች ዕድገትም ሆነ ግንባታ ያለውን ጠቀሜታ ግምት ውስጥ በማስገባት ነበረ ። በዛሬው ዝግጅታችን እንሆ፤ ሳይንስን ፣ሥነ ቴክኒክን ወደው ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ተምረው ከተመለሱ በኋላ፣ በአሁኑ ጊዜ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የሥነ-ቴክኒክ ተቋም ሙያዊ ትምህርት አቅራቢ(ሌክቸረር) በመሆን የሚያገለግሉትንና የፈጠራም ሆነ የምርምር አዲስ ግኝቶች ባለቤት በመሆን 2 ጠቃሚ ነገሮችን ለናሙና ሠርተው ያቀረቡትን አቶ ሙሉነህ ለማን አነጋግረናል። በቅድሚያ እማኝ ከሆኑት ባልደረቦቻቸው መካከል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ፣ የተማሪዎች አገልግሎት ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ተሾመ ይርጉ-----
አቶ ሙሉነህ ለማ፤ እስቲ ለናሙና ስላቀረቧቸው የሥነ ቴክኒክ የምርምር ውጤቶችዎ ምንነትና አገልግሎት ዘርዘር አድረገው ያስረዱን----
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ