የአዲስ ሆስፒታል ፕሮጀክት በአዲስ አበባ
ሐሙስ፣ የካቲት 14 2005ማስታወቂያ
በአሜሪካን ሃገር በተለያዩ የህሕክምና ዘርፎች የተሰማሩ ኢትዮ አሜሪካውያን ሐኪሞች አዲስ አበባ ውስጥ ሆስፒታል ለመገንባት ማቀዳቸውን አስታወቁ ። ሆስፒታሉን የሚገነባው የኢትዮ አሜሪካውያን ሐኪሞች ቡድን 3 አባላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለለግንባታው የሚያስፈልጋቸውን ቦታ መረከባቸውንና ግንባታውም ከ 6 ወር በኋላ እንደሚጀመር አስታውቀዋል ። ሐኪሞቹ እንዳሉት የሆስፒታሉ መገንባት በሃገር ውስጥ ህክምና የማይገኝላቸውን ሰዎች ችግር ያቃልላል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ