የአዮዲን እጥረት፤ እንቅርት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 8 2004ማስታወቂያ
በዚያዉ ልክ ከመጠን ሲያልፉ ወይም ሲያንሱ ደግሞ ችግር ይኖራል። ለምሳሌ በአዮዲን እጥረት ምክንያት ተግባሩ የሚስተጓጎለዉ የአንገት እጢ እንቅርት ሲያስከትል ይህም በመድሃኒት አለያም በቀዶ ጥገና ሊወገድ የሚችል የጤና ችግር ነዉ። አዮዲን የተሰኘዉን ንጥረነገር ዉሃ ዉስጥም ሆነ ጨዉ ዉስጥ ተቀላቅሎ ሊወሰድ ይችላል። በቀን ሃያ ሚሊ ሊትር አዮዲን መዉሰድ ከተቻለ፤ የአንገት እጢ በአግባቡ እንዲሰራ በማድረግ የእንቅርትን ስጋትን ለማራቅ ይቻላል ተብሎ ይታመናል። ለመሆኑ እንቅርት ሴቶችን ብቻ ነዉ የሚያጠቃዉ ወይስ ወንዶችም ይታይባቸዋል? ሳምንታዊ መሰናዷችን ጤናና አካባቢ የባለሙያ ማብራሪያ ይዟል። ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ