የ«አይ ኤስ» የጭካኔ ተግባር እና የብሪታንያ ውግዘት
ሰኞ፣ መስከረም 26 2007ማስታወቂያ
በብሪታንያ የሚኖሩ ሙስሊሞችም የበጎ አድራጎት ስራ ለማከናወን ወደ ሶርያ ተጉዞ የነበረው ሄኒንግን እንዳይገደል ፅንፈኛውን ቡድን ቢማፀኑም፣ ሰሚ ሳያገኙ ነበር የቀረው።ቡድኑ ይህንን አስከፊ የጭካኔ ተግባር የፈፀመው የብሪታንያ የጦር አይሮፕላኖች በ«አይ ኤስ» ወይም በእስላማዊ መንግሥት አንፃር በዩኤስ መሪነት በተጀመረው የጥቃት ዘመቻ መሳተፍ ከጀመረ በኋላ ነበር። ሄኒንግ ቡድኑ ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ አንገታቸውን ቀልቶ የገደላቸው ሶስተኛው የምዕራቡ ዓለም ተወላጅ ነበሩ።
ድልነሳ ጌታነህ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ