የአይ ኤም ኤፍ የኤኮኖሚ እድገት ጠቋሚ ዘገባ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 18 2008ማስታወቂያ
አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይ ኤም ኤፍ) በጎርጎሮሳዊው የ2015/2016 ከሰሀራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት የኢኮኖሚ እድገት ጠቋሚ ዘገባ አውጥቷል። በሪፖርቱ መሰረት ሀገራቱ ከሞላ ጎደል ያስመዘገቡት የኢኮኖሚ እድገት ከዛሬ 6ዓመት ወዲህ የታየ ዝቅተኛ እድገት ነው ። እንደ ዘገባው ነዳጅ አምራች የሆኑ የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት በእጅጉ የሚቀንሰ ሲሆን መካከለኛ ገቢ ያላቸው ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራትም ለአለም የሚያቀርቡት ሸቀጥ ገበያ መቀዝቀዙና እድገታቸውም ከ3.8% እንደማይበልጥ ተመልክቷል።ሆኖም ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው የአፍሪቃ ሃገራት መካከል ኮትዲቯር፣ኢትዮጵያና ታንዛንያ የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘግባሉ ብሏል አይ ኤም ኤፍ። እንደ ድርጅቱ በአማካኝ የ7% እድገት ይኖራቸዋል። ናትናኤል ወልዴ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ናትናኤል ወልዴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ