የአየር ጠባይ ለዉጥ ማካካሻ
ሰኞ፣ ጥቅምት 9 2002ማስታወቂያ
የአየር መለወጥ በድሃ ህዝቦች ላይ የሚያስከትለዉን ችግር በተመለከተም በአዉሮጳ ኅብረት ዉይይት ተካሂዷል። ኦክስፋም የተሰኘዉ ግብረሰናይ ድርጅት ከአዉሮጳ የልማት ኮሚሽን ጋ በመተባበር ባዘጋጀዉ በዚህ ዉይይት የአየር ጠባይ ለዉጥ በኑሯቸዉ ላይ ያስከተለዉን ጫና በእማኝነት ለማሳየት ከአዳጊ አገራት የተወከሉ አርሶ አደሮች ተገኝተዉ ምስክርነታቸዉን ሰጥተዋል። ይህን ተፅዕኖ ለመቋቋምም ከአዉሮጳ ኅብረት 35 ቢሊዮን ዩሮ በየዓመቱ እንደሚፈለግ ተጠቁሟል።
ገበያዉ ንጉሤ
ተክሌ የኋላ/ሸዋዬ ለገሠ