የአየርላንድ ግድያና የብሪታንያ ይቅርታ
ረቡዕ፣ ሰኔ 9 2002ማስታወቂያ
የብሪታንያ ወታደሮች በ1964 በአየርላንድ ሠላማዊ ሠልፈኞች ላይ ተኩስ ከፍተዉ ላጠፉት ሕይወት የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ኬሜሩን ትናንት በይፋ ይቅርታ ጠየቁ።«ጥቁሩ-እሁድ» ተብሎ በሚጠራዉ ዕለት የብሪታንያን አገዛዝ በመቃወም አደባባይ ከወጡ ሠላማዊ ሠልፈኞች መካካል አስራ-ሰወስት ሰዎች ተገድለዉ ነበር።ግድያዉ እቅከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እንዳነጋገረ ነዉ።ግድያዉንና ምክንያቱን እንዲያጣራ የቀድሞዉ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር የሰየሙት ኮሚሽን አስራ-ሁለት አመታት የፈጀ የምርመራ ዉጤቱን ትናንት ይፋ አድርጓል።በምርመራዉ ዉጤት መሠረት ወታደሮቹ ንፁሐን ሰዎችን ነዉ-የገደሉት።ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን ለደረሰዉ ጥፋት ይቅርታ ጠይቀዋል።መሳይ መኮንን ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
መሳይ መኮንን
ሂሩት መለሰ