የአውሽቪትዝ መታሰቢያ በአዲስ አበባ
ዓርብ፣ ጥር 22 2007ማስታወቂያ
በጀርመን ናዚ አገዛዝ ዘመን ከዛሬ 70 ዓመት በፊት በአውሮፓ በአይሁዳውያን ላይ በጅምላ የተፈጸመው ግድያ አዲስ አበባ ውስጥ ታስቧል ። በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጆአሂም ሽሚትና በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ወይዘሮ በላይነሽ ዜቫድያ በተገኙበት ትናንት በአፍሪቃ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ላይ ወደፊት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች እንዳይደርሱ መከላከልና ማስቆም የእያንዳንዱ መንግሥት ሃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተጠቁሟል ። በመታሰቢያው ላይ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮችና የአንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮችም መገኘታቸውን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘግቧል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ