የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ውጤት ሲገመገም
ሐሙስ፣ ሰኔ 4 2001ማስታወቂያ
የዛሬ ሳምንት ተጀምሮ እስካለፈው ዕሁድ ድረስ በሀያ ሰባቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በተካሄደው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ወግ አጥባቂዎች በድል ተንበሽብሸዋል ። በአንፃሩ የብሪታኒያው ሌበር ፣ የጀርመኑ ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ ፤ የፈረንሳዩ ሶሻሊስት ፓርቲ ፣ በታሪካቸው ታይቶ የማይታወቅ ሽንፈት ተከናንበዋል ። ከሰላሳ ዓመት አንስቶ ህዝቡ በቀጥታ ተወካዮቹን በሚመርጥበት በአውሮፓ ፓርላማ የህዝብ ዕንደራሴዎች ምርጫ ታሪክ እጅግ ዝቅተኛ ህዝብ ድምፅ በሰጠበት በዘንድሮው ምርጫ ቀኝ ፅንፈኞችና ፀረ የውጭ ዜጎች ፍልሰት አቋም ያላቸው ፓርቲዎችም ድል ቀንቷቸዋል ።
ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ