የአውሮፓ የአቶም ኃይል ማመንጫዎች ደህንነት
ማክሰኞ፣ መጋቢት 13 2003ማስታወቂያ
በከባዱ አደጋ መንስኤ ኤሌክትሪክ ሲቋረጥ የፉኩሽማው የኃይል ማመንጫ ጋኖችን ግለት የሚያበርዱ ማቀዝቀዣዎች ስራቸውን ማቆማቸው የከፋ አደጋ ማስከተሉ ፣ እንዲሁም በአንዳንዶቹ ጋኖች ፍንዳታዎች ተከስተው ከተቋሙ መርዛማ ጨረር ማፈትለኩ ከአቶም ኃይል የሚያመነጩ አገራትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አንቅቷል ። በተለይ የአቶም ኃይልን በሰፊው ጥቅም ላይ ያዋሉት የአውሮፓ ሀገራት ከጃፓኑ አደጋ በኋላ ተቋሞቻቸው የሚገኙበት ሁኔታ እንዲፈተሽና እና የፉኩሽማው መሰል አደጋ እንዳይደርስ በጋራ ለመከላከል በሰፊው እየመከሩ ነው ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ