1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት የሀምሳ ዓመት ጉዞ

ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2001

የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች እና የመሰረታዊ ነፃነቶች ጥበቃ ድንጋጌ አርባ ሰባት አባላት ያሉት የአውሮፓ መማክርት ሸንጎ ካፀደቃቸው እጅግ ጠቃሚ ድንጋጌዎች አንዱ ነው ።

https://p.dw.com/p/HAsG
የሽትራስቡርጉ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤትምስል AP
በርካታ አውሮፓውያን ፍትህ ሲሹ ፊታቸውን ወደ አውሮፓው ሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ማዞር ጀምረዋል ። የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቤቱታዎችን በመመልከት ላይ ያለው ሽትራስቡርግ ፈረንሳይ የሚገኘው የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት እ.አ.አ በ1950 የፀደቀውን የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ መሰረት አድርጎ እ.አ.አ በ1959 የተቋቋመ ፍርድ ቤት ነው ። ይኽው ድንጋጌ ቁጥራቸው ወደ ስምንት መቶ ሚሊዮን ለሚጠጋ ዜጎች ብቻ ሳይሆን በአባል ሀገራት ግዛት ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ መሰረታዊ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶችን ለማስጠበቅ የአውሮፓ ምክርቤት አባላት ቃል የገቡበት ዓለም ዓቀፍ ውል ነው ።