የአውሮፓ ኅብረት የባህር ኃይል ዘመቻ14 ታኅሣሥ 2001ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2001«ካርልስሩኸ» የተሰኘችው የጀርመን የጦር መርከብ፣ ከሶማልያ ጠረፍ ማዶ ከተሠማራው የአውሮፓው ኅብረት ፀረ-የባህር ላይ ውንብድና የጦር መረከቦች አጀብ ጋር ለመቀላቀል ዛሬ፣ ከጂቡቲ ወደ ምሥራቅ ተንቀሳቅሳለች።https://p.dw.com/p/GMAqፍራንትዝ ዮሰፍ ዩንግ፣ በጂቡቲ ወደብምስል APማስታወቂያ«የዘመቻው ተቀዳሚ ዓላማ የባህር ላይ ወንበዴዎችን እያሳደዱ እርምጃ መውሰድ ሳይሆን ማሥፈራራት ነው። ይሁን እንጂ የባህር ላይ ወንበዴዎቹ አደብ አልገዛ ካሉ፣የከረረ እርምጃ በመውሰድ፣በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸውን መርከቦች ማስለቀቅ፣ የወንበዴዎቹን ጀልባዎች ማስጠም፣ ተገቢ ይሆናል » የጀርመን የመከላከያ ሚንስትር ፍራንትዝ ዮሰፍ ዩንግ፣