የአውሮፓ ባንኮች የገንዘብ ዝውውር መረጃ ያስነሳው ውዝግብ
ሐሙስ፣ ጥር 27 2002ማስታወቂያ
ሚኒስትሮቹ ለአሜሪካን የሰጡት ይህ ፈቃድ ግን በአብዛኛዎቹ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም ። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ለዩናይትድ ስቴትስ መረጃ አሳልፎ ለመስጥት የተስማሙበት መንገድ ስምምነቱ የተደረገበት ወቅትና ሂደቱ እንዲሁም የግለሰቦችን ሚስጥር ተላልፎ እንዲሰጥ መፍቀዳቸውም በተለያየ አቅጣጫ ማወዛገቡን እንደቀጠለ ነው ። ከጎርጎሮሳውያኑ ታህሳስ 1 , 2009 ዓ.ም አንስቶ ከቀድሞው የላቀ የመወሰን ሥልጣን ያገኘው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ስምምነቱን በመጪው ሳምንት በሚካሄድ ድምፅ አሰጣጥ ሳያፈርሰው እንደማይቀር እየተነገረ ነው ።
ሂሩት መለሰ ፣ ነጋሽ መሀመድ