የአውሮፓ ህብረት ሩስያ ና የሶሪያ ጦርነት
ረቡዕ፣ ግንቦት 28 2005ማስታወቂያ
ለሶሪያ ጦርነት መፍትሄ የሚሻ ጉባኤ ጄኔቫ ውስጥ እንዲካሄድ ሩስያና ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረቡትን ሃሳብ እንደሚቀበል የአውሮፓ ህብረትም አስታውቋል ። የጄኔቩ ጉባኤ ሃሳብ አመንጪ ሩስያ በበኩሏ የሶሪያ ተቃዋሚዎች መከፋፈል ጉባኤው እንዳይሰምር አንዱ አደጋ ሊሆን እንደሚችል አሳስባለች ። በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ፑቲን የአውሮፓ ህብረት በሶሪያ ላይ የጣለውን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ማራዘም ባለመቻሉ ማዘናቸውን ገልጸዋል ። የአውሮፓ ህብረትና ሩስያ ትናንት በሶሪያ ጉዳይ ላይ አትኩረው ስላካሄዱት ውይይት የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን አነጋግሬዋለሁ ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ