የአውሮፓ ህብረትና ሩስያ
ዓርብ፣ መጋቢት 12 2006ማስታወቂያ
ትናንትናና ዛሬ በክሪሚያ ሰበብ የምዕራቡ ዓለምናየሩስያ ውዝግብ ተካሯል የተካሄደው የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ሩስያ ክሪሚያን ወደ ግዛቷ ለመቀላቀል መወሰኗን በማውገዝ በ12 ተጨማሪ የሩስያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ ጥሏል ፤ በውጭ የሚገኝ ሃብት ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስም አግዷል ። የሩስያ ምክር ቤት የክሪምያውን ህዝበ ውሳኔ ውጤት ተቀብሎ ክሪምያ ከሩስያ ጋር የምትቀላቀልበት ሂደት በተፋጠነበት ወቅት ላይ የተካሄደው የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጠንከር ያለውን የኤኮኖሚ ማዕቀብ ያስተላልፋል ተብሎ ነበር የተጠበቀው ። ጉባኤውን የተለታታለው የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ያቀርብልናል ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ