የአውሮጳ እና የአፍሪቃ ሀገሮች ትብብር
ረቡዕ፣ ኅዳር 8 2003ማስታወቂያ
የአውሮጳ ህብረት እና የአፍሪቃ ሀገሮች ጉባዔ በሊብያ መዲና ትሪፖሊስ ሊጀመር አንድ ሳምንት በቀረው ባሁኑ ጊዜ ከአፍሪቃ እና ከአውሮጳ ህብረት የተውጣጡ የልማት ርዳታ ጠበብትና የርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ባለፉት ሶስት ዓመታት የነበረውን የሁለቱን ቡድኖች ግንኙነት መለስ ብለው ገምግመዋል። ሀያ ሰባቱ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች እና ሀምሳ አራቱ የአፍሪቃ ሀገሮች የደረሱት ስምምነት ትልቅ ግምት የሚሰጠውና አዲስ ጅምር ይከፍታል ተብሎ የተነቃቃ ፈታኝ ፕሮዤ ቢሆንም፡ ሀይነር ኪዘል እንደሚለው፡ በቂ የህዝብ ትኩረት አላገኘም።
ሀይነር ኪዘል
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ