የአውሮጳ ህብረት እና የተገን አሰጣጡ ፖለቲካው
ማክሰኞ፣ መስከረም 12 2002ማስታወቂያ
የአውሮጳ ህብረት ኮሚስዮን ወደሀገራቸው ሊመለሱ ከማይችሉት መካከል ጥቂቶቹን ለመቀበል በስብሰባው ላይ ያቀረበውን ሀሳብ አባል ሀገራቱ ሚንስትሮች ደግፈው መቀበላቸውን ወቅታዊው የህብረቱ የሚንስትሮች ምክር ቤት ፕሬዚደንትን ስልጣን የያዘችው የስዊድን ሀገር አስተዳደር ሚንስትር ቶቢያስ ቢልስትሮም እና የህብረቱ ኮሚስዮን የፍትህና ደህንነት ጉዳይ ምክትል ኮሚሽነር ዣክ ባሮት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስረድተዋል። ከዚህ ሌላም ስደተኞቹ፡ ብቻቸውን ወደአውሮጳ የሚገቡ ልጆች ጭምር፡ ከሚመጡባቸው ሀገሮች ጋር ምክክር እንደሚያስፈልግ ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።
ገበያው ንጉሴ/አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ