1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት በኢራን ላይ ያሳረፈው ማዕቀብ

ሰኞ፣ ጥር 14 2004

የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ዛሬ በኢራን ላይ አዲስ ማዕቀብ እንዲጣል ወሰኑ።

https://p.dw.com/p/13oat
ምስል picture-alliance/dpa

ኢራን በአከራካሪው የአቶም መርሀግብርዋ ሰበብ የተፈጠረውን ውዝግብ ለማስወገድ የሚቻልበትን ዘዴ ለማፈላላግ ተጀምሮ ወደነበረው ድርድር እንድትመለስ ለማስገዳድ በማሰብ አሁን የተጣለው አዲሱ ማዕቀብ የኢራን ነዳጅ ዘይት ንግድ ላይ ያነጣጠረ ከመሆኑም በላይ የሀገሪቱ ማዕከላይ ባንክ ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ያዛል። የማዕቀቡን ውሳኔ ሀያ ሰባቱ የአውሮጳ ህብረት ሀገሮች ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በአንድ ድምፅ አሳልፈዋል። ህብረቱ ማዕቀቡን በአሁኑ ጊዜ ለማሳለፍ የወሰነበትን ምክንያት የብራስልሱን ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት ጠይቄው ነበር።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሰ