የአውማ ኦባማ እና የአይ ዌይ አስተያየት
ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2005ማስታወቂያ
ብዙ ባህሎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በሚነሱበት ጊዜ ያካባቢው ቋንቋዎች እና ባህሎችም ግንዛቤ ውስጥ የሚገቡበት አሰራር ወሳኝ ነው። ይህ ትምህርት የሚቀሰምበት ሂደት ነው፤ በዚሁ ረገድ ዝግጅታችሁ በጣም ጥሩ ነው። ሥርጭታችሁ ከሕዝቦች ጋ በሚደረግ ውይይት ላይ የተመሠረተ፡ እነሱንም ያሳተፈ እና ለሀሳባቸውም ትኩረት የሰጠ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። እና እንደማስበው ዶይቸ ቬለ ይህን እያደረገ ነው። መልካም ዕድል! »
ቻይናዊው አርቲስት አይ ዌይዌይ
ዶይቸ ቬለ ከተቋቋመ ዘንድሮ 60 ኛውን ዓመት ያከብራል። በነዚህ 60 ዓመታት ዶይቸ ቬለ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጠቃ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ሚና ተጫውቷል። በተለይ በቻይና የፕሬስ እና ሀሳብን የመግለጽ ነፃነትን ለማስፋፋት በተለይ የዶይች ቬለ የቻይና ቋንቋ ክፍል ከፍተኛ አገልግሎት አበርክቶዋል፤ ወደፊትም ከዚህ የበለጠ ሚና መጫወት እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ።