1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ ተጠናቀቀ

ዓርብ፣ ጥቅምት 11 2009

ለሁለት ቀናት የዘለቀዉ የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ ዛሬ ተጠናቀቀ። ጉባኤዉ ከታለመዉ ዉጤት ላይ ባይደርስም በዋናነት በኅብረቱ እና ካናዳ መካከል ነፃ ንግድ ስምምነት ላይ ያተኮረ ድርድር አካሂዷል።

https://p.dw.com/p/2RXIM
EU Gipfel in Brüssel - Bundeskanzlerin Angela Merkel
ምስል Getty Images/AFP/E. Dunand

Q&A EU Summit - MP3-Stereo

ወደ አዉሮጳ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር መቀነስ ላይ ባለመዉ ዉይይቱም በተለይ ከአፍሪቃ የሚፈልሱትን ለማገድ የጀመረዉን ጥረት ለማጠናከር ተስማምቷል። ከዚህም ሌላ ኅብረቱ የሩሲያ እና የአዉሮጳን ግንኙነትን በተመለከተ ሊያካሂድ ያለመዉ ዉይይት፤ ሞስኮ በሶርያ ጦርነት ዉስጥ ባላት ሚና ላይ ማተኮሩ ተነግሯል። ጉባኤዉ ሲጠናቀቅ የተካሄደዉን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለዉ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ