የአዉሮጳ ኅብረት ምስረታ 60ኛ ዓመት
ዓርብ፣ መጋቢት 15 2009ማስታወቂያ
የኅብረቱ መሪዎች ማምሻዉን ከሮማዉ ርዕሰ ሊቃነ- ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር እንደሚገናኙ ታዉቋል። በነገዉ እለት 27 ቱ የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት መሪዎች ተሰብስበዉ ኅብረቱ የ 60 ዓመት ጉዞና ያገጠሙትን ተግዳሮቶች በመገምገም የወደፊቱን የጉዞ አቅጣጫና ግብ የሚያሳይ አዲስ ሰነድ ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከመሪዎቹ ስብሰባ በተጓዳኝ የኅብረቱ ደጋፊ ኃይሎች የጠሩት ታላቅ አዉሮጳ አቀፍ የድጋፍ ሰልፍም በሮማ አደባባዮች ይደረጋል። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሤ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ