የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ጉባኤ
ዓርብ፣ ጥቅምት 15 2006ማስታወቂያ
ሆኖም ጉባኤዉ አስቀድሞ በያዛቸዉ የመነጋገሪያ ነጥቦች ላይ ከመነጋገር ይልቅ ትኩረቱ በጣልያኗ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ ያለፈዉ የስደተኞች ህይወት እንዲሁም የአሜሪካን የስለላ ተቋም የአዉሮጳ መሪዎችን የስልክ ግንኙነት ሳይቀር ጠልፏል በሚለዉ መወሰዱ ነዉ የተገለጸዉ።
በዉሳኔያቸዉም የሜዲትራኒያን ባህርን እያቋረጡ ወደአዉሮጳ ለመግባት የሚሞክሩ ሕገ ወጥ ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎችን የመከታተል ርምጃ እንዲወሰድ ከሚለዉ አንስቶ ድንበር ጠባቂዎች ህይወት የማዳን ተግባር እንዲያከናዉኑ የሚለዉ ሲጠቀስ፤ ስለላዉን በሚመለከት ደግሞ መሪዎቹ የሁለትዮሽ ግንኙነትን እንደሚጎዳ በማመልከት ከዋሽንግተን ማብራሪያ ጠይቀዋል። ጉባኤዉ ሲጠናቀቅ የተካሄደዉን ጋዜጣዊ ጉባኤ የተከታተለዉ የብራስልሱ ወኪላች ገበያዉ ንጉሤን ስለጉዳዩ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ