1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት ለኢትዮጵያ የ130 ዩሮ ድጋፍ ሰጠ

ሐሙስ፣ ጥር 16 2011

የኢትዮጵያዉ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከዳቮስ ስዊዘርላንድ ጉብኝት በኋላ ሃሙስ እለት በአዉሮጳ ኅብረት ጽ/ቤት መቀመጫ ብረስልስ ተገኝተዉ ከኅብረቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ከዶናልድ ቱስክና ከኅብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ጆን ክላውድ ጆንከር እንዲሁም ከአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ከፌዴሪካ ሞግሄርኒ ጋር ተወያይተዋል።

https://p.dw.com/p/3C8bq
Brüssel EU Besuch Premierminister Abiy Ahmed Äthiopien
ምስል Getty Images/AFP/E. Dunand

የጠ/ሚ ዐቢይ የአዉሮጳ ኅብረት ስኬታማ ጉብኝት

በኢትዮጵያ ዘላቂ ኃይልን ለማመንጨት፣ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክና ስራ ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ አዉሮጳ ኅብረት 130 ሚሊየን ዮሮ ድጋፍ እንደሚሰጥ ተገለፀ። ዳቮስ ስዊዘርላንድ ላይ በሚካሄደዉ 49ኛዉ የዓለም ኤኮኖሚ መድረክ ላይ ትናንት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በአዉሮጳ ኅብረት ድ/ቤት መቀመጫ ብረስልስ ተገኝተዉ ከኅብረቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ቱስክ እና ከኅብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ጆን ክላውድ ጆንከር ጋር ከተወያዩ በኋላ 
በኢትዮጵያ ዘላቂ ኃይልን ለማመንጨት፣ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክና ስራ ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ ከኅብረቱ ለማግኘት ስምምነቶችን ማካሄዳቸዉን ቦታዉ ላይ የሚገኘዉ የብረስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ገልፆልናል። 
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ፤ ከኅብረቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ቱስክ ጋር ባደረጉት ዉይይት የጋራ ጥቅምን ለማረጋገጥ በጋራና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸዉም ተነግሮአል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ፌዴሪካ ሞግሄርኒ ጋርም ተወያይተዋል።   

Brüssel EU Besuch Premierminister Abiy Ahmed Äthiopien
ምስል picture-alliance/AP Photo/F. Seco

አዜብ ታደሰ 

ተስፋለም  ወልደየስ