1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳና የጀርመን መንግሥት ርዳታ ለኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 19 2008

የአዉሮጳ ኅብረትና የጀርመን መንግሥት ለኢትዮጵያ የግብርና ልማት ፕሮጀክት መርጃ የሚሆን የ 3,8 ሚሊዮን ርዳታ ለመለገስ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ተስማሙ።

https://p.dw.com/p/1JW8a
Flagge der EU
ምስል picture alliance/Wolfram Steinberg


ርዳታዉ በተለይ ማኅበራዊና አካባቢያዊ ተኮር ለሆነ የግብርና ልማት ማስፋፍያ ፕሮጀክት እንደሚዉል ተገልጾአል። የኢትዮጵያ የግብርና ልማት የመሬት አስተዳደር ኤጀንሲና በግብርና ሚኒስቴር ተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ መምሪያ ለፕሮጀክቶቹ ተግባራዊነት ኃላፊዎች ናቸዉ ተብሎአልም። ፕሮጀክቶቹ ማኅበራዊ ጠቀሜታ ያላቸዉና ለአካባቢያዊ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጡ ተጠያቂነትና ግልፅነት ያላቸዉ እንዲሁም የአካባቢዉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የግብርና ልማቶችን የሚያግዙ እንደሆኑም ተነግሮአል።

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ