የአዉሮጳ ሕብረት ርዳታ ለአፍሪቃ ቀንድ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 16 2009ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት በድርቅ ለተጎዱ የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ሐገራት ሕዝብ መርጃ 66.5 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚረዳ አስታወቀ።ሕብረቱ ትናንት እንዳስታወቀዉ ርዳታዉ በርካታ ሕዝብ ለተራበባቸዉ ለኢትዮጵያ፤ለሶማሊያ፤ለደቡብ እና ለሰሜን ሱዳን የሚከፋፈል ነዉ።በሕብረቱ መግለጫ መሠረት ካጠቃላዩ ርዳታ በጦርነት የወደመችዉ ደቡብ ሱዳን 28 ሚሊዮን ዩሮ በማግኘት የመጀመሪያዉን ሥፍራ ስትይዝ፤ በርካታ ሕዝብ የተራበባት ኢትዮጵያ ሁለተኛዉን ከፍተኛ ርዳታ ታገኛለች።22,5 ሚሊዮን ዩሮ።ሶማሊያና ሰሜን ሱዳን እያንዳዳቸዉ 8 ሚሊዮን ዩሮ ያገኛሉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ