የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት እና ኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ ጥር 12 2008ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት እንደራሴዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ይፈፀማል ሥለሚባለዉ የሠብአዊ መብት ጥሠረት በቀረበ የዉሳኔ ሐሳብ ላይ እየተወያዩ ነዉ።ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ዉስጥ ዛሬ ለሚመክረዉ ምክር ቤት የቀረበዉ ረቂቅ ዉሳኔ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ በኦሮሚያ መስተዳድር ለተቃዉሞ አደባባይ የወጡ ሰዎችን ገድሏል፤ በሺሕ የሚቆጠሩትን አስሯል፤ የጋዜጠኞችን መብት ሳይቀር ይርግጣል የሚሉ ሐሳቦችን ያካተተ ነዉ።የምክር ቤቱ የሶሻሊስት እና የሊቢራል ወይም ለዘብተኛ ፓርቲ እንደራሴዎች ያረቀቁት ሐሳብ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ጋር ያለዉን ግንኙነት ዳግም እንዲያጤን የሚጠይቅ ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን ሥለ ረቂቁ ጠይቄዉ ነበር።
ገበያዉ ንጉሴን
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሠ