የአዉሮጳ ሕብረት ማዕቀብና ሶሪያ
ረቡዕ፣ ሰኔ 15 2003ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት ሚንስትሮች በሶሪያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ዛሬ ወስነዋል። ብሪታንያና ፈረንሳይ ባቀረቡት ዝር ዝር መሠረት ሕብረቱ ለሶሪያ መንግሥት ጋር የንግድ ግንኙነት አላቸዉ ባላቸዉ አራት ኩባንዮች ላይ ማዕቀብ ጥሏል።የሶሪያን ፖለቲካዊ ቀዉስ ለማስወገድ ግን የሐገሪቱ መንግሥት ከተቀናቃኞቹ ጋር ሚንስትሮቹ «እዉነተኛ» ያሉትን ድርድር እንዲያደርግ አሳስበዋል።የሶሪያ መንግሥት የሕብረቱን ዉሳኔ የቅኝ ገዢዎች አስተሳሰብ በማለት ነቅፎታል።ወደ ስቱዱዮ ከመግባቴ በፊት የብራስልሱ ወኪላችንን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ