የአዉሮጳ ሕብረትና ቱርክ
ዓርብ፣ መጋቢት 9 2008ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት እና የቱርክ ባለሥልጣናት «ሕገ-ወጥ» የሚሏቸዉ ሥደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዳይገቡ ለማገድ ከዚሕ ቀደም በተስማሙበት ነጥብ ላይ የሚያደርጉት ድርድር በስምምነት አጠቃለዋል። የሕብረቱ አባል ሐገራት መሪዎች እና የቱርክ ጠቅላይ ሚንስትር ከዚሕ ቀደም ያደረጉትን ስምምነት ዛሬ አጽድቀዋል። ሁለቱ ወገኞች ቱርክ እንዲሟላላት ካቀረበቻቸዉ ነጥቦች በአንዳዶቹ ላይ ባለመግባባታቸዉ ረዘም ላሉ ሰዓታት ስምምነቱን ሳይፈራረሙ ሲደራደሩ ነበር የዋሉት። በሌላ በኩል የሁለቱ ወገኖች መሪዎች ተስማሙም ተፋረሱ ዓላማቸዉን የመብት ተሟጋቾች እየተቃወሙት ነዉ።ሥምምነቱ ከመፅደቁ ጥቂት ቀደም ብሎ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ