የአዉሮጳዉ ህበርት በጋዛና የጋዝ ቀዉስ27 ታኅሣሥ 2001ሰኞ፣ ታኅሣሥ 27 2001የዘንድሮዉን የአዉሮጳያን ዓመት የ2009ኝን የስድስት ወራት የአዉሮጳ ህብረት የፕሬዝደንትነት ስልጣን የተረከበችዉ የቼክ ሪፑብሊክ በሩሲያና ዑክሬን መካከል በተከሰተዉ የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ዉዝግብ ሳቢያ በተከተለዉ ችግርና እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለችዉ ወታደራዊ ጥቃት ገና ከጅምሩ ተወጥራለች።https://p.dw.com/p/GSUdዑክሬንን የሚያቋርጠዉ የጋዝ ቧምቧምስል APማስታወቂያሩሲያ የምዕራብ አዉሮጳ ዋነኛዋ ጋዝ አቅራቢ ስትሆን አብዛናዉ ጋዝዋ የሚያልፈዉ ዑክሬንን አቋርጦ በተዘረጋዉ ቧምቧ አማካኝነት ነዉ። ሞስኮ ከአዲሱ የአዉሮጳ ዓመት መባቻ አንስታ ለዑክሬን የምታቀርበዉን ጋዝ በዋጋ ባለመግባባትና በዉዝፍ እዳ መዘዝ አቋርጣለች። ሌሎችም በርምጃዉ ተነክተዋል።