የአንድነት አመራር አባላት ስሞታ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 3 2005ማስታወቂያ
የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት አዲስ አበባ በሚገኘው ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የታሰሩ የቀድሞ የድርጅቱ አመራር አባላትን እንዳይጠይቁ መከልከላቸውን አስታወቁ ። በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙትን አባላቶቻቸውን ለመጠየቅ ከፍተኛ የአመራር አባላቱ ወደ ማረሚያ ቤቱ ቢሄዱም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ ስለሌሉ መግባት አትችሉም ተብለው ሳይጠይቋቸው መመለሳቸውን የድርጅቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ ፣ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል ። ሃላፊው ክልከላው በህግ ጥበቃ ሥር ስለ ሚገኙ ዜጎች በህገ መንግሥቱ የተደነገገውን አንቀፅ የሚጥስ መሆኑን ተናግረዋል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሰ