የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መግለጫ8 ሐምሌ 2001ረቡዕ፣ ሐምሌ 8 2001መሪው ወይዘሪት ቡርቱካን ሚዴቅሳ የታሰሩበት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፓርቲው ህገ ደንብ ውጭ እየተንቀሳቀሱ ናቸው ያላቸውን ሀያ አንድ መስራችና ነባር የአመራር አባላቱን ማገዱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ።https://p.dw.com/p/IqChማስታወቂያታደሰ ዕንግዳው ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ከታገዱት አባላት ውስጥ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ዶከተር ሽመልስ ተክለ ፃዲቅና አቶ ወሮታው ዋሴ ይገኙበታል ። ዛሬ የታገዱት አባላት በበኩላቸው የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ በስልጣን ባልጓል ሲሉ ከሰዋል ። ታደሰ እንግዳው ፣ ሂሩት መለሰ፣ሸዋዬ ለገሠ