1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ አንዳርጋቸዉ መታሠርና ተቃዉሞዉ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 1 2006

የብሪታኒያ መንግሥት ዜጋው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከየመን ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸው በእጅጉ እንዳሳሰበው ለኢትዮጵያ መንግሥት ማንሳቱን አስታወቋል። የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመን ላይ መያዝና ወደ ኢትዮጵያ መወሰድን በመቃወም ዛሬ በተለያዩ ሐገራት ሠልፍ ተደርጓል።

https://p.dw.com/p/1CYMO
Karte Äthiopien englisch

ኢትዮጵያዉን አደባባይ ከወጡባቸዉ ከተሞች ለንደን አንዷ ናት። እዚሕ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንም የግንቦት ስባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ እንዲፈቱ በመጠየቅ ፍራንክ ፈርት ወጥ ተሠልፈዉ ነዉ ያረፈዱት።የሠልፉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት ሠልፈኛዉ አቶ አንዳርጋቸዉን በሕገ-ወጥ መንገድ ይዛ ለኢትዮጵያ አሳልፋ ሠጥታለች ያላትን የመንን ሲያወግዝ፤ብሪታንያ ደግሞ ዜጋዋን እድታስፈታ ጠይቋል።ከዚሕም በተጨማሪ ሰልፈኛዉ የመን ቆንስላ አጠገብ ተገኝቶ የየመንን ባንዲራ አቃጥሎ፤ የየመን መንግሥት ፈጸመዉ ያለዉን ምግባር አዉግዟል።ለብሪታንያ ቆንስላ ደግሞ አቤቱታዉን አቅርቧል። የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ በስፍራዉ ተገኝቶ ዘገባ አድርሶናል። ነጋሽ መሐመድ ከፍራንክፈርት ከሠልፉ አስተባባሪዎች አንዷን ወይዘሮ አሳየሽ ራዉሼልን በሥልክ አነጋግራቸዉ ነበር።

ድልነሳ ጌታነህ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ