የአትሌት ኃይሌ ገሥላሴ ጋዜጣዊ መግለጫ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 19 2008ማስታወቂያ
በኦሎምፒክ እና በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ውድድሮች በርካታ ድሎችን በማስመዝገብ የሚታወቀው አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ኢትዮጵያ በርዮው ኦሎምፒክ ማግኘት የሚገባትን ውጤት አላገኘችም ሲል ቅሬታውን ገለፀ ። የዚህ ችግር መንስኤም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደራሽን አሠራር መሆኑን ኃይሌ ከቀድሞ አንጋፋ አትሌት እና አሠልጣኛ ቶሎሳ ቆቱ ጋር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰሰጠው መግለጫ አስታውቋል ።በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ቶሎሳ ቆቱ ፣ ሌላው አብይ ችግር የአትሌቶች የቡድን ሥራ መቅረት እና የአትሌቶች እና የአሰልጣኞች መራራቅ መሆኑን ተናግረዋል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ